News
Navigation
Vacancy
We have 1 guest online

Kombolcha City Administration Mayor Office::Home

አቶ ደነቀ ምትኩ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከመዲናችን አዲስ አበባ በስተሰሜን 375 ኪ.ሜ ፣ ከባህር ዳር በ505 ኪ.ሜ ፣ ከጂቡቲ ወደብ በ513 ኪ.ሜ እንዲሁም ከደሴ በስተደቡብ በ23 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፤አጠቃላይ የቆዳ ስፋቷም 124.5 ኪ.ሜ ስኩየር ይሆናል፡፡

ኮምቦልቻ የሚለውን ስያሜዋን ከጣሊያን ወረራ ጋር ተያይዞ እንዳገኘች የሚነገርላት ከተማችን ከ126144 በላይ የህዝብ ቁጥር ታስተዳድራለች፡፡ በሀይማኖት መቻቻል ተምሳሌትነቷም ትታወቃለች፡፡ ከተማችን በኢንዱስትሪ መናገሻነት ከተመረጡት ጥቂት ከተሞች አንዷ ስትሆን በአሁኑ ሰአት የፌደራልና የክልሉ መንግስት በሰጧት ልዩ ትኩረት በርካታ መሰረተ ልማቶች እየተገነቡና አገልግሎት እየሰጡ ከመሆኑም ባሻገር የከተማችንን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻሉት ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የደረቅ ወደብ አገልግሎት፣ የአውሮፕላን ማረፊያ ፣የባቡር መስመርና ሌሎች ዋና ዋና ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በኢንቨስትመንት ዘርፍ 253 የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች እንደ ሀገር የተቀመጡ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሽግግር ግቦችን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ድርሻቸውን ለመወጣት እየሰሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ከተማችን በዚህ ዘርፍ ሰፋፊና ምቹ መሬቶችን በማዘጋጀት አልሚ ባለሀብቶችን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች፡፡

በቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት በኩል በርካታ ሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚ መሆን የጀመሩ ሲሆን አንዳንዶቹም ወደ መካከለኛ ባለሀብትነት በመሸጋገር ላይ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይ በትምህርትና ጤና ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት፣ልዩ ልዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትና የቱሪዝም ልማትን ለማሳደግ የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፎች ተመጋጋቢ የልማት ውጤቶችን ለማስመዝገብ ሠፊ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም የድረ-ገጻችን ደንበኛ በመሆን የምትሰጡን አስተያየትና ድጋፍ ለልማታችን መፋጠን ወሳኝ በመሆኑ አስተያየታችሁን እንድትለግሱንና ወደ ከተማችን በመምጣት እንድታለሙ እንጋብዛለን፡

 

 
English (United Kingdom)
Most read content
About website